የብሮድካስት ባለስልጣን “ገለልተኛ ኤክስፐርቶች” “ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠና ምንጫቸው የማይታወቅ”

የብሮድካስት ባለስልጣን “ገለልተኛ ኤክስፐርቶች” “ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠና ምንጫቸው የማይታወቅ”

0
306

የብሮድካስት ባለስልጣን “ገለልተኛ ኤክስፐርቶች” “ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠና ምንጫቸው የማይታወቅ” ብሎ ለከሳሾቻችን የፈረደላቸው የክስ ነጥቦች መካከል ለምሳሌ፥

1-ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የህይወቴ ትዝታዎች፡ ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ” በሚለው መጽሃፍ ውስጥ በግልጽ የጻፈው ጉዳይ። በምርጫ 2005 ወቅት ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ በወቅቱ የነበሩትን ጳጳሳት ለማናገር ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ጋር ሲሄድ፣ ዋናው ጳጳስ ፕሮፈሰር ብርሃኑን መስቀል አሳልሞ ፕሮፌሰር መረራን እንደዘለለው የግል ትዝብቱን ጽፏል ፕሮፌሰር መረራ። መምህር ሃይለሚካኤልም በሰላሌው ንግግሩ በግልጽ የጠቀሰው ይህንኑ ነጥብ ቢሆንም፣ “ገለልተኞቹ” የብሮድካስት ዳኞች ግን ይሄንን ነጥብ “ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠና ምንጫቸው የማይታወቅ” በሚል ፈርጆ ለከሳሾች ፈርዶላቸዋል።

2-ጃዋር መሃመድ በቅርቡ ባደረገው የdiaspora tour ላይ የኦርቶዶክስ ቄሶች መስቀል ጭምር ይዘው የተቃውሞ ሰልፍ መውጣታቸው፣ ቸርች ውስጥ ጭምር ህዝብ ለተቃውሞ እንዲወጣ የፖለቲካ ቅስቀሳ ማድረጋቸው፣ እነዚሁ ቄሶች ግን ለሚደግፏቸው የፖለቲካ ሰዎች ቆባቸውን እንኳ ሳያወልቁ የድጋፍ ሰልፍ መውጣቸው ባደባባይ ያለ ጉዳይና ሁሉም የሚያውቀው እውነት ነው። መምህር ሃይለሚካኤልም ይህኑኑ ያደባባይ ሚስጥር ነበር የተናገረው። “ገለልተኞቹ” የብሮድካስት ዳኞች ግን ይሄንንም ነጥብ “ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠና ምንጫቸው የማይታወቅ” በሚል ፈርጆ ለከሳሾቻችን ፈርዶላቸዋል።

3-ሌለኛውና አስቂኙ ክስ ደግሞ “…ቤተክርስቲያን ያንድ ቡድን የፖለቲካ ኢምባሲ መሆን የለባትም” የሚለው የአቶ ሃይለሚካኤል አስተያየት “የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ ነው” በሚል ለከሳሾቻችን የተፈረደው ነው። ይታያቹ እንግዴ … የተጠቀሰውን አስተያየት የተናገረው መምህር ሃይለሚካኤል ራሱ ከሳሾቹ የሚከተሉትን ሃይማኖት ነው የሚከተለው። ማለትም OMN ላይ አስተያየቱን የሰጠው ሰውም ሆነ አስተያየቱን ስላልወደዱት OMNን የከሰሱት ሰዎች የአንድ እምነት ተከታዮች ናቸው። በዚህ እውነታ ላይ ቆሞ ለሚመለከት ማናቸውም ሰው፣ የተጠቀሰው አስተያየት “የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ ነው” ተብሎ እንዴት ነው ሊበየን የሚችለው?

በመሰረቱ ብሮድካስት ባለስልጣኑ “ኤክስፐርቶች” የከሳሾቹን የክስ ማመልከቻ እንዳለ አጸደቁት እንጂ የጨመሩትም ሆነ የቀነሱት ነገር የለም።

OMN በዚህ ኢንቲሚዴትድ አይሆንም። የሚታወቅበትን የህዝቦች ድምጽ የመሆን ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል።

#Ethiopia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here