ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች።

ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች።

0
338

ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች

ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ የተፋሰሱ አገራትን በማይጎዳ መልኩ እና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በማክበር የመጠቀም መብቷን አሳልፋ እንደማትሰጥ መንግስት አስታውቋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ እና ሂደት እንዲሁም የድርድር ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የምትገነባው ሙሉ መብቷ ስለሆነ እና ግድቡን መገንባት የሌላ ሀገርን ደጅ ጥናት የሚጠይቅ አለመሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታውቀዋል፡፡

የሕዳሴ ግድብ እየተገነባ ያለው በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ፣ ከኢትዮጵያ በሚፈስስ ወንዝ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሃብት መሆኑንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የገለፁት።

በመግለጫው ላይ የተገኙት የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ሀገራችን ነዳጅ እና ሰፊ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ስለሌላት የተፈጥሮ ሀብቷን ለመጠቀም ግድ ይላታል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ግድቡን በተሻለ ፍጥነት መገንባት ላይ ትኩረት መደረጉንና ለዚህም ብቃት ያላቸው እና ተመሳሳይ ትልልቅ ግድቦችን የመሥራት ልምድ ያላቸው ኮንትራክተሮች ተመድበው እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

Via #EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here